አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በኢንስቲትዩቱ ተከበረ
March 15, 2022
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ111 ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል ለ46ኛ ጊዜ የእየተከበረ የሚገኘው አለምአቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ በኢንስቲትዩቱ የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ፣የማኔጂመንት አባላትና የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በተገኙበት መጋቢት 6/2014ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ አዳራሽ ተከበረ፡፡
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር የፕሮግራሙ መክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በሴቶች ላይ የሚደርሱ ማንኛውንም አስቸጋሪ ነገሮች በጋራ በመተባበር የማስቆም ስራ የሁሉም ድርሻ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ የሴቶችን ጥቃት ከመከላከል አንጻር የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በርካታ ችሮችን ፊት ለፊት በመጋፍጥ እየሰሩ መሆኑን በማስታዎስ በቀጣይም የተሻለ ስራ ለመስራት የበኩላቸውን ድርሻ የሚወጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡