አዲስ የምግብ ደህንነት ላቦራቶሪ ተከፈተ
April 14, 2021
የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዉስጥ የሚገኘዉ የምግብ ሳይንስ እና ኒዉትሪሽን ዳይሬክቶሬት በዘመናዊ መልኩ የተሰራ የምግብ ደህንነትና የምግብ ማይክሮ ባዮሎጂ የምርምር ኬዝቲም ላብራቶሪ የኢንስቲትዩቱ ዋና እና ምክትል ዳሬክተሮች በተገኙበት አስመረቀ ፡፡ ይህ ላብራቶሪ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነዉ ላብራቶሪ ሲሆን ረጅም አመታት ሲሰራበት የቆየ ህንፃ በማርጀቱና ጠባብ በመሆኑ ለስራ አመቺ እና ከወቅቱ ና ከጊዜዉ ጋር የሚሄድ ባለመሆኑ ላብራቶሪዉ አዲስና ዘመናዊ ላብራቶሪ መገንባት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በዘመናዊ መልክ ሊሰራ እንደተቻለ፣ ላብራቶሪዉ አገልግሎት የዉሃ ወለድ እና የዉሃ ወለድ ወረርሽኝ ላይ እንደሚሰራ የችግሩ መነሻ ምክንያት ላይ ምርመራ አና ምግብ ና ዉሀ ጥራት ና ደህንነት ምርመራ እንደሚያካሂድ በምረቃ ፕሮግራሙ ተገልጽዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ላብራቶሪዉን ለመገንባት ብዙ ጊዜ አንደፈጀ አና ወደ 7 ሚሊዮን ብር አንደፈጀ ገልፀዋል፡፡