አገር አቀፍ አረንደጓዴ የአሻራ ቀን በኢንደስቲትዩቱ ሰራተኞች

July 30, 2019
አገር አቀፍ የአረንጓዴ የአሻራ ቀንን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሰራተኞችና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በጉለሌ ክፍለ ከተማ በእንጦጦ ተራራ ላይ በመሰማራት ከ5 ሺ በላይ
የሚሆኑ ችግኞችን የተከሉ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑት ሰራተኞች ደግሞ ከጤና ሚኒስቴር ሰራተኞች
ጋር በመሆን በሞጆ አካባቢ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
በቀጣይም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ከጉለሌ ክ/ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት
ጽ/ቤት ጋር በገቡት የውል ስምምነት መሰረት የተከሏቸውን ችግኞች ይንከባከባሉ፡፡