አፍላቶክሲን (Aflatoxin) አጠቃላይ በአለም አቀፍ የግብይት ደንብ እና ጤና ላይ የሚያመጣውን ተጽእኖ እስመልክቶ በተዘጋጁ ጥናቶች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
May 12, 2023
በኢንስቲትዩቱ የምግብና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በተገኙበት አፍላቶክሲን ( Aflatoxin) አጠቃላይ በአለም አቀፍ የግብይት ደንብ እና ጤና ላይ እያስከተለ ያለውን ተጽእኖ እስመልክቶ በተዘጋጁ ጥናቶች ላይ በኢንስቲትዩቱ የስልጠና ማዕከል ግንቦት 3/2015 ዓ.ም ውይይት ተካሄደ፡፡
የውይይቱ ዋና አላማ በአፍላቶክሲን (Aflatoxin) ላይ የተጠኑ አለም አቀፍና አገር አቀፍ ጥናቶች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የተለያዩ አለማቀፍና አገር አቀፍ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን ሰፊ ውይይት በማድረግ እንደ ኢትዮጵያ አፍላቶክሲንን (Aflatoxin) አስመልክቶ መደረግ ስለሚገባቸው የመፍትሄ ሂደቶች አስተያየት እና አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብ እና የመድሃት ቁጥጥር ባለስልጣን ሃላፊዎች፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማኔጂመንት አባላትና በለሙያዎች፣ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች እና የአጋር ድርጅት ሃላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡