ኢትዮጵያ 453600 የኮቪድ-19 ክትባት እርዳታ አገኘች
July 19, 2021
የአሜሪካ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብ የ453600ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ-19 ክትባት በእርዳታ መለገሱን ተገለጸ፡፡
ኢትዮጵያ ዛሬ ሃምሌ 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከአሜሪካ መንግስት ቃል ከተገባው 1.2 ሚሊዮን ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ውስጥ የ 453600 መጠን ያለው ክትባት አዲስ አበባ ቦሌ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት ደርሶ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካው አምባሳደር ክብርት ጊታ ፓሲ (Geeta Pasi)፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳሬክተርና የኮቪድ-19 ምላሽ ዋና አስተባባሪ አቶ አስቻለዉ አባይነህ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት
ርክክብ የተደረገ ሲሆን ይህ ክትባት ከሌሎች የሚለየው በአንድ ዙር ብቻ የሚሰጥ የኮቪድ-19 ክትባት መሆኑ ነው፡፡
የጤና ሚኒሰትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ ሲሆን ይህ ክትባት የኮቪድ-19 ቫይረስን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ ላይ ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረው ገልፀዋል፤ ሚኒስትሯ አክለው ይህን ክትባቱን ላበረከተው ለአሜሪካ መንግስት ምስጋና አቅርበዋል።