ኢንስቲትዩቱን ያለፈውን በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ከሐምሌ 21-24/2013 በአዳማ ከተማ ኃይሌ ሪሶርት ገመገመ
August 2, 2021
የኢንስቲትዩቱ ዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ እና አቶ አስቻለው አባይነህ፣ የዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች፣ የጽ/ቤት እና የማዕከላት ሃላፊዎች በተገኙበት የኢንስቲትዩቱን ያለፈውን በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን ከሐምሌ 21-24/2013 በአዳማ ከተማ ኃይሌ ሪሶርት ገመገመ፡፡
በግምገማው ወቅት ሁሉም የስራ ክፍሎች በበጀት ዓመቱ የነበራቸውን አፈጻጸም በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በዚህም ላይ በአፈጻጸሙ ወቅት ያጋጠማቸውን ተግዳሮቶች ምርጥ ተሞክሮዎች አቅርበው በነዚህም ላይ ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በአመራሮችም ቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
የዚህ መድረክ ዋና ዓላማም በባለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት እና መልካም ልምዶችን በመቃኘት የሚቀጥለው ዓመትን ዕቅድ ለማዳበር ወሳኝ ግብዓቶችን ለመውሰድ ያለመ ነበር፡፡