ኢንስቲትዩቱ ለሚቀጥለው አስር ዓመት ያቀደውን ስትራቴጂያዊ ዕቀድን ከግብ ለማድረስ

ኢንስቲትዩቱ ለሚቀጥለው አስር ዓመት ያቀደውን ስትራቴጂያዊ ዕቀድን ከግብ ለማድረስ ያስችል ዘንድ በየደረጃው ለሁሉም ሰራተኞች ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ የመጀመሪያው ዙር ለአስተዳደር ሰራተኞች መሰጠት ተጀምሯል።
ዶ/ር አማር ባርባ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሀላፊ የመድረኩን መርሀ ግብር እና አጠቃላይ አላማ እንዳስተዋወቁትበመድረኩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዋና ተግባራት፥ ነባራዊ ሁኔታዎችና የወደፊት ዕቀዶች እንደሚዳሰሱ ጠቅሰዋል።
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ለዕቅዱ መሳካትም እኩል ሀላፊነት እንዳለበት ከገለጹ በኋላ የቅርብ ጊዜ ክስተት የነበረውን የኮቪድ 19 ወረርሽ ምላሽን ሁሉም ሰራተኛ በእኩል ቁርጠኝነት በመንቀሳቀሱ አመርቂ ውጤት መገኘቱንና በአፍሪካ ደረጃ የሚያስመሰግን ስራ መሰራት መቻሉን ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ ከኢንስቲትዩቱ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በተጨማሪ የመንግስት አገልግሎት ዘርፍ የለውጥ ፍኖተ ካርታ፥ ስለ ስነ ምግባር እና ሞራል ምንነት፥ የመንግስት ሰራተኞች መተዳደሪያ ደንብና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገልጋይ ተኮር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የቀረቡ ሲሆን የፓሰተር አካባቢ ማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጣቢያ ማስተባበሪያ ሀላፊ ዋና ሳጅን አንድነት በበኩላቸው ስለ ወንጀልና ወንጀል መከላከል ጉዳዮች አቅርበዋል። በነዚህም ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል።