ኢንስቲትዩቱ በኤሌክትሮኒክ የመንግስት የግዢ ስርዓት (E-GP) ያካበተውን ልምድ ከቶጎ ለመጡ የልዑካን ቡድን አካፈለ
May 18, 2023
የመንግስት ግዢና ንብረት ባለስልጣን በ2015 የበጀት ዓመት ከፌዴራል ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኤሌክትሮኒክ የመንግስት ግዢ ስርዓት አጠቃቀም ላይ ባሳየው ውጤታማ አፈጻጸም መመረጡን ተከትሎ ከቶጎ መንግስት ለተላኩ ሰባት ባለሙያዎች ያካበተውን ልምድ አካፍሏል፡፡ በመድረኩ የኢንስቲትዩቱበየግዥና ፋይናንስ ዳይሬክተር አቶ አሰፋ ሀብቴ ንግግር በማድረግ የልምድ ልውውጡ የከፈቱ ሲሆን ኢንስቲትዩት ያገኘውን መልካም አፈጻጸምና በሂደቱም ያጋጠሙትን መሰናክሎች እንዴት እንደተወጣቸው አስረድተዋል፡፡
የግዥ ክፍል ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘላለም ገብረየሱስም የአፈጻጸም ሂደቶቹን በጽሁፍ ለልኡካን ቡድኑ ያቀረቡ ሲሆን ይህንንም መሰረት በማድረግ የልዑካን ቡድኑ የተለያዩ ጥያቄዎች፣ ሀሳቦችና አስተያየቶች ያነሱ ሲሆን ለነዚህም የኢንስቲትዩቱ የግዥ አጽዳቂ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር አብረሃም አሊና የግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት አባላት በጋራ በመሆን ተገቢውን ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡