ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች የሶስተኛ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዲያገኙ ማስቻሉ ተገለጸ።
July 28, 2023
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች የሶስተኛ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን እንዲያገኙ አስችሏል።
ከኢንስቲትዩቱ የሰው ሀብት አመራር ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከ20 በላይ የኢንስቲትዩቱ ባለሙያዎች ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በዘንድሮው ዓመት አለምነሽ ኃይለማርያም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን የተቀበሉ ሲሆን ባለፉት ዓመታትም አዱኛ ወዬሳ፣ ደስታ ካሳ፣ ገረመው ጣሰው፣ አበበ አሰፋ፣ አዳሙ በላይ፣ ማስረሻ ተሰማ፣ አረጋሽ ሳሙኤል፣ ኢሳያስ ክንፈ፣ ሚኒሊክ ደምሴ፣ ያሬድ ደበበ፣ ቢቂላ ነጋ፣ በለጠ ተግባሩ፣ ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ አትኩሬ ደፋር፣ ጌታቸው ኢቲቻ፣ ደረጀ ንጉሴ እንዲሁም አይናለም ላቀው ሶስተኛ ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል።