ኢንስቲትዩቱ 2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድን በማቀድ ላይ ይገኛል
June 15, 2023
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ከኢንስቲትዩቱ ዳይሬክቶሬቶች እና ጽ/ቤቶች ጋር በመሆን የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድን በማቀድ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የዕቅድ ዝግጅት ላይ ሁሉም የስራ ክፍሎች በየዘርፋቸው በቡድን በመሆን ዕቅዳቸውን ከተሻሻለው የኢንስቲትዩቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ አንጻር ካቀዱ በኋላ የህንኑ አቅርበው ውይይት ተደርጎበት በግብዓቶች ዳብሮ ለማኔጅመንት እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡
የስራ ክፍሎቹ ዕቅዳቸውን ማቀድ ከመጀመራቸው በፊት መድረኩን ዶ/ር አማር ባርባ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ የመክፈቻ ንግግር ካደረጉ በኋላ የዕቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ሞገስ የተሻሻለውን የኢንስቲትዩቱን ዕቅድ በጽሁፍ አቅርበው እንዴት መታቀድ እንዳለበትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥተዋል፡፡