እንኳን 1,442ኛው ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

July 20, 2021
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1,442ኛው ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል፡፡
የኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል ስናከብር እርቀትን መጠበቅ፣የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም፣እጅን በሳሙናና በውሃ መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር በማፅዳት ወደ ስግደት በምንሄድበት ወቅት የግል መስገጃ መጠቀም ፣ የኮቪድ-19 ክትባት በመከተብ የኮቪድ-19 ቫይረስ እንድንከላከል እንዲሁም የቀጣዩን ዓመት ኢድ-አል አድሐ (አረፋ) በዓል በጋራ እንድናከብር ዛሬ ላይ እንድንጠነቀቅ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያሳስባል፡፡
ዒድ ሙባረክ!!
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
#COVID19Ethiopia
#ዒድሙባረክ
#EIDMUBARAK