ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታ አምጪ ተህዋስያን የመድሀኒት ፈዋሽነትን የመቋቋም/Zoonotic AMR Surveillance/ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተከናወነ

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የብሔራዊ አንድ ጤና ስልት የተህዋሲያን መድሀኒት መላመድ መከላከያ እቅድን እየተገበረች ትገኛች።
እንደ አገር የሰው ጤና፣ የእንስሳት ጤና እና የአካባቢ ጤና እንደ አንድ የጤና ስርዓት በባለድርሻዎች ትብብር እየተሰራ እንደሆነ የተናገሩት ዶ/ር መሳይ በተለይ ም የተህዋሲያን መድሀኒት መላመድ (Antimicrobial Resistance) የተያያዙ ጉዳዮች በጤና፣ በምግብ ደህንነት እና በኢኮኖሚ የሚያደርሱትን ዘርፈ ብዙ ጉዳት በመገንዘብ በአንድ ጤና አቅጣጫ ላይ በመመስረት ሁሉም ባለድርሻዎች በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል። የግንዛቤ መስጫ መድረኩም ይህን ለማጠናከር እንዲያግዝ የታሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ እና ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ገረመው ጣሰዉ ደግሞ የተመረጡ መረጃዎችን በመሰብሰብ፣ እንቅስቃሴዎችን በመተንተን እና መረጃውን በማካፈል እውነተኛው የችግሩ መጠን እንዲታወቅ መስራት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ይህ የአንድ ጤና በተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና በኢትዮጵያ በሰው፣ በእንስሳት፣ በእንስሳት ተወዕጾ/ምግብ እና በአከባቢ መስተጋብር ላይ ፀረ ተህዋሲያን በጀርሞች መላመድ/የመቋቋም ማስረጃ ለማመንጨት /Zoonotic AMR Surveillance፡ One Health inaction) ላይ ያተኮረ ግንዛቤን ማሻሻል፣ በትግበራ እቅድ እና መረጃ አሰባሰብ ላይ የጋራ መረዳትን ማዳበር እንዲሁም የተሻለ እውቀት ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ እና ትኩረት የሚሹ ሀሩራማ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት የእንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዲቭዥን ኃላፊ እና የፕሮጀክቱ አስተባበሪ የሆኑት ዶ/ር ይመር ሙሉጌታ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የዞኖቲክ ኤኤምአር ቅኝት ፕሮጀክት አተገባበር እና መረጃ ማሰባሰብን ለማጠናከር፡ “አንድ ጤና” በተግባር አጠቃላይ እይታ ላይ እና በኢትዮጵያ የ Zoonotic Bacteria ብሔራዊ ፀረ-ተህዋስያን በጀርሞች መለመድ/የመቋቋም ቅኝት ጥናት የትግበራ መመሪያ/ዕቅድ አንድ ጤና በድርጊት ላይ ያተኮረ መወያያ ሰነድን አቅረበዋል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ የብሔራዊ የእንስሳት ምርቶች እና የግብአት ጥራት መሞከሪያ ማዕከል፣ የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የአማራ ክልል የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ፣ የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት እና የትግራይ ክልል የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ፣ የሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የኦሮሚያ የሕብረተሰብ ጤና እና ምርመር ኢንስቲትዩት እና የአሰላ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡