ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለጤና ባላሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያ ተሰጠ
January 29, 2020
የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ማብራሪያና ገለጻ ጥር 20/2012 አደረገ፡፡
የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻው ያስፈለገበት ዋና ምክንያት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና እየተካሄደ ያለውን ቅድመ ዝቅጅት በተቀናጀና በጋራ ስራዎችን ለመስራት እንዲሁም ሕብረተሰብን የማንቃት ስራ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ለማድረግለ የሚያስችል ግንዛቤ ለመፍጠር ነው፡፡
በገለጻው ወቅት ቫይረሱን ለመቆጣጠር የአለም ሃገራት፣ የአለም ጤና ድርጅት እያደረጉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴ፣ ከመንግስታዊ እና መንግስታዊ ከልሆኑ አካላት ጋር መሰራት ስላለባቸው ጉዳዮች፣ የጤና ባለሙያዎች ሕብረተሰቡ ከበሽታው እራሱን እንዲጠብቅ ከማንቃት አንጻር መሰራት የሚገባቸውን ስራዎች፣ በበሽታው የተጠረጠሩ ሰዎች የሚለዩበትን ሁኔታ፣ እንደ አስፈለጊነቱ በማገገሚያና በጽኑ ህሙማን ማዕከል በአግባቡ የሚታከሙበትን ሁኔታ፣ የቫይረሱን መተላለፊያ መንገዶች እና ምልክቶቹ ምን እንደሆኑ በዝርዝር ለባለሙያዎቹ የግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተሰጥቷል፡፡