ኮቪድን ለመከላከል የተለያዩ ድጋፎች እየተደረጉ ይገኛሉ
December 11, 2020
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የኮቪድን ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ የተለያዩ ቁሳቁሶችና ግብዓቶችን ለኢንስቲትዩቱ የህብረተስብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማእከል አስረከበ፡፡
ድርጅቱ በ157 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፉ በብረት የተሰሩ 3 የተለያዩ የኮቪድ ቁሳቁስና ግብዓቶች ለማከማቻነት የሚያገለግሉ 320 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው መጋዝኖችን በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ በመገንባት ከማስረከቡም በላይ ለተለያዩ ሆስፒታሎች የኮቪድ ቫይረስን ለመከላከል የሚያገለግሉ የጤና ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ከዶ/ር ኢስቴኮን ዌር አማሞ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጋር ስለ ተደረገው አጠቃላይ ድጋፍ እና ኮቪድን ከመከላከል አንጻር ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ ስለሚሰሩ አጠቃላይ የእንቅስቃሴ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በድርጅቱ በኩል ስለተደረገው በርካታ ድጋፍ በኢንስቲትዩቱና በጤና ሚኒስቴር ስም ምስጋና በማቅረብ በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ የተገነቡትን እስቶሮች ከድርጅቱ ዳይሬክተር ጋር በመሆን ጎብኝተዋል፡፡