ዓለም አቀፍ የበሽታ ጫና ሲምፖዚየም እየተካሄደ ነው
የኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ የጤና መረጃ ማደራጃ ፣ ቅመራና ትንተና ማእከል ከ Institute for Health Metrics and Evaluation (IHME) project ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ የበሽታ ጫና ሲምፖዚየም (GBD Symposium) ከጥቅምት 21 እስከ 23/2016 ዓ/ም በኢንስቲቲዩቱ የስልጠና ማዕከል በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የሲፖዚየሙ ዋና ዓላማ ለድጋፍ ሰጪ አካላት ለብሔራዊ ብሎም በክልሎች ደረጃ ያለዉን የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለማጠናከር እና የመረጃ ተደራሽነትን እንዲሁም መጋራትን ለማመቻቸት ለሚደረጉ ድጋፎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር፤ ለተሻሻለ አገራዊ እና ሃጉራዊ የበሽታ ግምቶች እና አካባቢያዊ ትንታኔዎችን ለማበልፀግ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡
ዶ/ር መሳይ ሀይሉ የኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በሲምፓዚየሙ የመክፍቻ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው እንደገለጹት ይህ ሲምፓዚያም በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና በIHME የትብብር ስራዎችና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ከመሆኑም በተጨማሪ በሚደረገው ውይይት የጋራ ስራዎች የሚመቻቹበት እንዲሁም ሳይንሳዊ መረጃዎችን ለፖሊሲ አውጪዎች ለውሳኔ የሚሆኑ ግብዓቶች የሚፈልቅበት ጉባኤ እንደሚሆን እምነቴ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የIHME project እና የአጋር ድርጅት ተወካዮች ሲምፓዚየሙን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች እየቀረቡ ከመሆናቸውም በላይ በቀጣይም በዋና ዋና አገራዊና ክልላዊ የበሽታ ጫናዎችን አስመልክቶ የፓናል ውይይቶች የሚካሄዱ መሆናቸውን ከመድረኩ ተገልጻል፡፡
በአገር ዉስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎች፤ የክልል ጤና ቢሮና የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች እንዲሁም አጋር አካላት በሲምፖዚየሙ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡