ዓመታዊ ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (IHR/SPAR)ግምገማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳ/ር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት የአለም አቀፍ የጤና ደንብ ፈራሚ አገር መሆኗን ጠቅሰው እያንዳንዱ አባል ሀገር አለም አቀፍ የጤና ደንቦች ትግበራን በተመለከተ ለዓለም የጤና ጉባዔ (WHA) በየዓመቱ የራሱ አመታዊ ግምገማ (SPAR/State Party Self-Assessment Annual Reporting) በማድረግ ሪፓርት ማቅረብ ይኖርበታል በማለት የገለፁ ሲሆን ይህ ዓመታዊ የአባል ሀገራት የራስ ግምገማ የህዝብ ጤና አደጋዎችን እና የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮችን ለመለየት ፣ ለመገምገም ፣ ለማሳወቅ ፣ ሪፖርት ለማድረግ እና ምላሽ ለመስጠት የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑን አብራርተዋል።
የአለም አቀፍ የጤና ደንቦች የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ፈይሳ ረጋሳ እንደተናገሩት በአለም አቀፍ የጤና ደንቦች ስር፣ አባል ሀገራት ለአለም አቀፍ አሳሳቢ ጉዳዮች÷ የህዝብ ጤና ጉዳዮችን ለመቆጣጠር እና ምላሽ ለመስጠት አነስተኛውን ዋና አቅሞችን የማዳበር እና የመጠበቅ ግዴታ አለባቸው። ዶ/ር ፈይሳ አክለውም የአለም አቀፍ የህዝብ ጤና ደህንነትን በማረጋገጥ ረገድ የአለም አቀፍ የጤና ደንቦች ስኬት የሚወሰነው በሁሉም አባል ሀገራት በሚኖረው ሙሉ አተገባበር፣ አፈፃፀም እና ተገዢነት ላይ ነው ብለዋል።
በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ ግምገማ ላይ የተለያዩ ሴክተሮችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፍ የሚገኙ ሲሆን ለቀጣይ 2 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።