የሄፓታይቲስ ሲ ( hepatitis C ) የምርመራና የህክምና አገልግሎትን በኢትዮጵያ ለማስፋትና የመከላከል ስተራቴጂ የሚነድፍ ዴስቲን (DESTINE) የተባለ የምርምር ፕሮገራም ሁለተኛ አመት አውደ ጥናት ተካሄደ
ይህ ህዳር 15 12ዐ1ዐ የተካሄደው አወደ ጥናት ዓላማው የሄፓታይቲስ ሲ ( hepatitis C) ቫይረስ ላይ ያተኮረ የምርመራና ህክምና አገልግሎት ፍላጎትን በኢትዮጵያ ላማስፋትና ውጤታማ የሆነ የመከላከል ስትራቴጂ ለማጎልበት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በምርምር የትብብር ማዕቀፍ ፕሮግራሙን ለመገምገም ታቅዶ የተዘጋጀ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ ነው፡፡
አውደ ጥናቱን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ሲሆኑ ዶ/ር ጌታቸው ጥሪ ለተደረገላቸውን የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተቋቋመበትን አላማና በአዲሱ አደረጃጀት አራት ዋና ዋና ተግባራትን ኢንዲያከናውን በአዋጅ የተሰጡትን ሃላፊነትቶች አስረድተዋል።
“የሕብረተሰብ ጤና አደጋን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ተግባራትን መምራትና ማስተባበር፣ ቅድሚያ ትኩረት በሚሰጣቸው የሕብረተስብ ጤናና ስነ ምግብ ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ የምርምር ፕሮገራምና ስተራቴጂ ማካሄድ፣ በጤና ላቦራቶሪ አቅም ግንባታና የሪፈራል የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ፣ እና ብሄራዊ የዳታ ቋት አስተዳደር፤ የመረጃ ቅመራና ትንተና ማካሄድ” በማለት ዶ/ር ጌታቸው የኢንስቲትዩቱን ኃላፊነቶች ገልፀዋል።
ዶ/ር ጌታቸው አያይዘውም ዴስቲን የምርምር ፕሮግራም በአለም ደረጃና በሀገራችን ደረጃ የሄፓታይቲስ ሲ እና የሄፓታይቲስ ቢ መንስዔነት በማህበረሰቡ ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ በዓለም ደረጃ 354 ሚሊዮን ህዝብ የሄፓታይቲስ በሽታ ጋር እንደሚኖሩና ከዚህም ውስጥ 3.2. ሚሊዮን ህጻናትና አዋቂዎች የዚሁ በሽታ ተጠቂዎች መሆናቸውን በንግግራቸው አመላክተዋል፡፡
በመግለጽ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ በመቀጠል ያስቀመጠውን ግብ እንዲያሳካ አሳስበዋል፡፡፤
ዴስቲን (DESTINE) የሄፓታይቲስ ሲ ( hepatitis C) ቫይረስ ኢንፌክሽን መጠንና ስፋት በኢትዮጵያ ምን እንደሚመስልና የበሽታውን ጥልቀት በኢፒዴሞሎጂና በሞዴልንግ ቴክኒኮች በመደገፍ የምርመራውን ሂደትና የህክምና አሰጣጡን በእንግሊዝ ሀገር የተቀመረውን ልምድ ወደ ኢትዮጵያ በማምጣትና ተግባራዊ ለማድረግ የፖሊሲ አውጭውን በመከላከል ስትራቴጂው ዙሪያ ለመምከር ዘርፈ ብዙ አካላትን ያሳተፈ ፕሮግራም ሲሆን በሀገራችን የሚታየውን የበሽታውን አደጋ ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ ፕሮግራም ነው።
በመጨረሻም ዶ/ር ጌታቸው ከውጭ ሀገርና ከሀገር ውስጥ በምርምር ትብብር ማዕቀፍ የምርምር ትስስር ፈጥረው ፕሮግራሙን እየመሩና እያገዙ ያሉትን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት የመጡትን ተመራማሪዎች፣ የልማት አጋሮችን እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካላትን ከልብ በማመስገን – ዴስቲን DESTINE) የምርምር ፕሮገራም ዎርክሾፕ በይፋ ሥራውን መጀመሩን አብስረዋል፡፡
በዚህ ምርምር ፕሮግራም ላይ የተሳተፉት ባለድርሻ አካላት ከእንግሊዝ ሀገር የዱንዴ ዩኒቨርሲቲ ( Dundee Bristol, Universities) ከእስራኤል Hebrew University፣ ከአዲስ አበባ፣ የጎንደር፣ የመቀሌ፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ፤ የኢትየጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የአርማር ሃንሰን የምርምር ኢንሲቲትዩት የተውጣጡ ናቸው።