የሕብተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦትና የሕብረተሰብ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለሚዲያ ባለሙያዎች ተሰጠ
የኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና ቅኝት እና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክቶሬት የሕብረተሰብ ጤና ስጋት ተግባቦትና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዲቪዥን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚዲያ አካላትን ሚና ለማሳደግ እና በሚዲያ አካላት በኩል ማህበረሰቡ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ለተለያዩ የሚዲያ ባለሙያዎች የጤና ስጋት ተግባቦትና የሕብረተሰብ ተሳትፎ ስለጠና ከሰኔ 25 እስከ 27/2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ሰጠ፡፡
ዶ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጡትን ኃላፊነት በዝርዝር የገለጹ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የሚያከናውናቸውን በርካታ ስራዎች ለማሕበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ብሎም ስለ ጤና አደጋዎች የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር በእቅድ የተደገፉ ስራዎችን ከሚዲያ አካላት ጋር በመቀራረብ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው ኢንስቲትዩቱ ለሚዲያ ባለሙያዎች ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የሚዲያ ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ እና በሚዲያ ድርጅቶች መካከል ስላሉ የጋራ ስራዎች ፣ ስለሚታዩ ክፍተቶችና መቀረፍ ስለሚገባቸው ቁልፍ ጉዳዩች እንዲሁም በቀጣይ በጋራ ስለሚከናወኑ ስራዎች አስመልክቶ በርካታ ጥያቄዎች ያቀረቡ ሲሆን ለተነሱት ጥያቄዎች ደ/ር መልካሙ አብቴ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ተገቢውን ምላሽ ሰጥተዋል፤ በቀጣይ መሰራት ስለሚገባቸው የጋራ ስራዎችም መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡