የመንግስት ፋይናንስ ፤የንብረት፤ የግዠእና የውሰጥ ቁጥጥር ስርዓትን አስመልክቶ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው
የመንግስት ፋይናንስ ፤የንብረት፤ የግዠእና የውሰጥ ቁጥጥር ስርዓትን አስመልክቶ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው
እንደ ሀገር በሁሉም ተቋማት ውሰጥ ለዘጎች የሚሰጡ የተለያዩ የግንዛቤ ማሰጨበጫ መድረኮችና አቅም መጎልበቻ ተግባራት ባለው ሀብት ላይ ተጨማሪ እሴት እንደተጨመረ ይቆጠራል፡፡ የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ መሰረት በማድረግ የኢንስቲትዩቱ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ከገንዘብ ሚኒስቴር ኢንስፔክሽን ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግስት ፋይናንስ ስርዓትን አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ከታህሳስ 14 እስከ 16/2015 ዓ.ም ለኢንስቲትዩቱ የተለያዩ ሞያ ላይ ለተሰማሩ ሰራተኞች 3ኛው ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ የመንግስት ንብረትን ብክነት ለመከላከል በኢንስቲትዩቱ ውጤታማ የንብረትና የፋይናንስ አስተዳደር፣ የፋይንንስ ሪፖርት እንዲሁም የግዥ አስተዳደር፤ በአጠቃላይ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው፡፡
አቶ ለሜሳ ጉደታ የኢንስቲትዩቱ የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በስልጠናው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት እንደተናገሩት የውስጥ ኦዲት ለመንግስትም ሆነ ለግል ተቋማት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ በአንድ ተቋም ላይ ስራዎች ከተሰሩ በኋላ የማረጋገጥ እና ስራዎች ከመሰራታቸው አስቀድሞ ስጋትን መሰረት ያደረገ ለቀጣይ ጥንቃቄ ችግሮችና ስጋቶች እንዲቀንሱ ግንዛቤን ሊያስጨብጡ የሚያስችሉ የምክር አገልግሎቶች መስጠት ዋናው የውስጥ ኦዲት ተግባራት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ስለ መንግስት ፋይናንስ ስራዓት ያላቸውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመወያየት እሰከ 3 ዙር ለ122 ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠት መቻሉንና በቀጣይም ሁሉም ሰራተኛች ስልጠናውን እንዲገኙ ለማድረግ በሞጁል ደረጃ አዘጋጅቶ ስልጠና ለመስጠት ዳይሬክቶሬቱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ለሜሳ አያይዘው ተናግረዋል፡፡
አቶ ዮሐንስ እጅጉ የገንዘብ ሚኒስቴር ኢንስፔክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ስልጠናውን ሲሰጡ እንደገለጹት የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር በመንግስት የአስተዳደር እርከኖች ውስጥ የፕሮግራም በጀት፣የሂሳብ አያያዝ ፣ የመንግስት ግዥን፣የንብረት አስተዳደር እና የውስጥ ኦዲት ተግባራት ትስስርን እንዲሁም ቅንጅት የሚያሳይ በመሆኑ የተቋማት ባለሙያዎች እነዚህን በተሻለ መንገድ ግንዛቤ በመፍጠር ውጤታማ ስራዎችን ማስመዝገብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ተሳታፊዎች ከስልጠናው በኋላ የፋይናንስ አስተዳደርን፣ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓትን፣ የውስጥ ኦዲት ሚና እና የተለያዩ የፋይናንስ ተግባራት በተሻለ መልኩ ተገንዝበው በኢንስቲትዩቱ ውጤታማ ስራዎች ማስመዝገብ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ከተሰጠው ስልጠና መረዳት ተችሏል፡፡