የመድሀኒት ብግርነትን በጋራ መከላከል እንዲሚገባ ተገለጸ
November 22, 2023
“ፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድ በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ለ 9ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ እየተከበረ ሲሆን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም የግንዛቤ የማስጨበጫ ሳምንቱን ምክንያት በማድረግ የኢንስቲትዩቱ የማኔጂመንት አባላት እና አጋር አካላት በተገኙበት ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ።
በመድረኩም የመክፈቻ ንግግሮችና ፀረ-ተህዋሲያን መድሀኒቶች በጀርሞች መላመድን አስመልክቶ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ችግሩን በመከላከል ደረጃ የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡