የመጀመሪያ ዙር AVoHC SURGE ሰልጣኞች ተመረቁ
የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአለም ጤና ድርጅት እንዲሁም ከአፍሪካ ተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር (Africa CDC) ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት፣ የመለየት እና ምላሽ አቅም ማሻሻያ ስልጠናን ያጠናቀቁ 100 ዘርፈ ብዙ ባለሙያዎችን በዛሬው ዕለት በሐዋሳ ከተማ አስመረቁ።
ወ/ሮ ነኢማ ዜኑ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ዝግጁነት እና አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በምርቃት ስነ ሰርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ሰልጣኞቹ የተመረጡት ከተለያዩ ዘርፎች ሲሆን የተመረጡትም ለዚሁ በተቋቋመው ኮሚቴ ሲሆን በአጠቃላይ ስልጠናው 33 ቀናት የወሰደ እንደሆነና ቀጣዩ ዙርም በኦክቶበር እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ በበኩላቸው ተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላቹህ በማለት ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች እየተጠቃች መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ የጤና አደጋዎች በመከሰት ላይ እንደሚገኙ በመጥቀስ ስልጠናውም ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን አስረድተዋል።
ከዶ/ር ጌታቸው በመቀጠልም ዶ/ር ፓትሪክ አቦክ ከአለም ጤና ድርጅት እና የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ም/ል ኮሚሽነር ዶ/ር ነሲቡ ያሲን በስነስርዓቱ ላይ መለዕክት የየበኩላቸውን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የጤና ሚኒሰቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጀ ድጉማ ደግሞ የስነስርዐቱ መጨረሻ ላይ የ መዝግያ ንግግር በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል።
ዶ/ር ደረጀ ሀገራችን የጤናውን ስርዓት ለማጠናከር እምቅ አቅም ያላት ሲሆን ይህንንም ለመጠቀም እንደዚህ አይነት ስልጠናዎች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማሰተባበሪያዎች በተጠናከረ መንገድ በመቋቋም ላይ መሆናቸው በመስኩ ያለውን እንቅስቃሴ እንደሚያጠናክረው ገልጸው ለስልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ያደረጉትን አጋር አካላት ሁሉ አመስግነዋል።
ይህ ስከልጠና በአጠቃላይ ለ700 ዘርፈ ብዙ ባለሙያዎች ለመስጠት በእቅድ ተይዟል።