የምርምር ፅሁፎችን በድህረገፅ ማስተናገድ ተጀመረ
November 23, 2023
በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የሳይንሳዊ ምርምር ስነምግባር ጽ/ቤት ለሚታተመው ጆርናል የምርምር ፅሁፎችን በድህረገፅ ለመቀበል፣ ለመገምገም እንዲሁም ለማሳተም የሚያስችል ዌብ ሳይት አበልፅጎ ስራ ላይ ማዋሉን በዛሬው ዕለት በይፋ አስታውቋል:: ድ/ቤቱ ይህንኑ ባስታወቀበት ፕሮግራም ላይም ለተመራማሪዎች ስለ ዌብሳይቱ ገለፃ የተሰጠ ሲሆን በተነሱ ሀሳቦች ላይም ውይይት ተካሂዶባቸዋል::
ዌብሳይቱን በሚከተለው ማስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል::
https://ejphn.ephi.gov.et