የሬዚልየንስ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ
May 21, 2021
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መልሶ ማቋቋም እና ሬሲሊየንስ ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከዓለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የማይበገር የጤና ስርዓት ለመፍጠር የአሰልጣኞች ስልጠና በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ ሰልጣኞች ከኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እጅ የእውቅና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡በእለቱም አቶ አስቻለው ለሰልጣኞቹ ዋናው የሰለጠኑትን ወደ ታች ማውረድ እንዳለባቸው እና ወደፊትም እንደዚህ አይነቱ ስልጠና በሁለተኛ እና በሶስተኛ ደረጃ እንደሰጥ የሚደረግ ቢሆንም የህንን ለማድረግ ግን ጊዜ የሚፈጅ እንደመሆኑ እስከዛ ግን የማይበገር የጤና ስርዓት ለመገንባት የነሱ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸው ለዚህ ስልጠና እውን መሆን ከመጀመሪያው ጀምሮ ትብብር እና ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩትን የዓለም የጤና ድርጅት፣ ዩኒቨርስቲዎችንን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል፡፡