የሶማሊያ የጤና ቡድን ኢንስቲትዩቱን ጎበኘ
የ2019 ዓመታዊ የአለም አቀፍ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች ማህበር ስብሰባን ምክንያት በማድረግ በስዊድን ሃገር የሕብረተሰብ ጤና ተቋም አስተባባሪነት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሶማሊያ ሃገር የጤና ባለሙያዎች እና የዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጎበኙ፡፡
የጉብኝቱ ዋና አላማ የሶማሊያ ሃገር የጤና ባለሙያዎችና የመንግስት ተወካዮች በኢትዮጵያ ያለውን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመጎብኘትና የልምድ ተሞክሮ በመውሰድ በሃገራቸው ጠንካራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለማቋቋም ተፈልጎ ነው፡፡
በተደረገው የአንድ ቀን ጉብኝት ሰፊ ውይይትና ገለጻ የተደረገ ሲሆን የኢንስቲትቱን ዋና ዋና የስራ ክፍሎች፣በሃገር አቀፍና በኢንስቲትዩቱ የሚያድረጉትን የላቡራቶሪ አገልግሎት እና ከጥራት አንጻር የተሰሩ በርካታ ስራዎች፣ ኢንስቲትዩቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የሚስራቸውን የተለያዩ ስራዎች ምን እንደሚመስሉ፣ሆስፒታሎችን ከመደገፍ አኳያ እና የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በመቆጣጠር ደረጃ የተከናወኑ ተግባራትንና አጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ የተሰሩ የምርምር ስራዎች በዝርዝር ገለጻ ተደርጓል፡፡
የኤች አይቪ እና ቲቢ እንዲሁም የምግብና የስነ-ምግብ ሳይንስ ምርምር ላቡራቶሪዎችን የጎበኙ ሲሆን በተደረገላቸው ገለጻና በአካሄዱት ጉብኝት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ማግኘታቸውንና ኢንስቲትዩቱ በአፍሪካ ትልቁን የምሳሌነት ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑን ከማረጋገጣቸውም በላይ በሃገራቸው ጠንካራ የብሕረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመገንባት የሚያስችል የመጀመሪያ ረቂቅ ለመንግስታቸው ለማቅረብ ሚያስችል ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሱማሊያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚገነባው በስዊድን ጤና ተቋም ድጋፍ ነው፡፡
የሶማሊያ ሃገር የጤና ሚኒስቴር ሃላፊዎች፣የጤና ባለሙያዎች እና የዩኒቨርሲቲ ምሁራን በአጠቃላይ 12 ልኡካን ጉብኝት አድርገዋል፡፡