የሶስተኛ ዙር የካውንት ዳውን የጥናት ውጤቶች ለግምገማ ቀረቡ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥርዓተ ጤና ምርምር ዳይሬክቶሬት በእናቶች፣ በጨቅላ ህፃናት እና ልጆች የጤና ሽፋንን ለማሳደግ ብሎም በጤናዉ ዘርፍ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት አቅርቦት እና ፍትሀዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጥናታዊ ፅሁፎች ከህዳር 2-3/2017 ዓ.ም ለግምገማ አቀረበ::
ዶ/ር አደራጀዉ መኮንን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር እንዳስረዱት የቀረቡት ጥናት ግኝቶች በእናቶች የቅደመ፣ የወሊድ እና በድህረ ወሊድ የጤና አገልግሎት እና ሽፋን ጥራትን ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
በእለቱም የጤና ተቋማት የእናቶችና እና ልጆች ጤና፤ የቤተሰብ እቅድ እና የክትባት አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ዝግጁነት ላይ የተገኘ ውጤቶች ላይ፣ በተለይም የሰለጠኑ ባለሞያዎች፣ የአሰራር መመሪያዎች ስለመኖራቸው የጤና አገልግሎት ለመስጠት የህክምና ግብዓቶች የዲያግኖስቲክ አቅም ስለመኖሩ እንዲሁም መድሃኒቶች አቅርቦት ላይ የተገኘው የፍተሻ ውጤት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡
ባለፉት20 ዓመታት በጤናው ዘርፍ በእናቶች እና ልጆች ጤና ላይ የተገኙ ውጤቶችን የሚገመግም ሲሆን አስቻይ ሁኔዎች በተለይም ከመንግስት ቁርጠኝነት ከፖሊሲዎች እና በስትራቴጂክ አፈፃፀም ከሀብት አሰባሰብና አጠቃቀም ቀልጣፋና አይበገሬ የስርዓተ ጤና ከመገንባት፣ የግል ዘርፍ በጤናው ላይ ያለውን ድርሻ ከማጎልበት እንዲሁም ከመረጃ አያያዝና አጠቃቀም የተገኙ ውጤቶች ላይ እንዲሁም በጤና ሴክተሩ ጥራቱን የጠበቀነ ፍትሃዊ ተደራሽነት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችንም ለመቀነስ በተሰጡ ምክረ ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዶባቸዋል ፡፡
በተጨማሪም መረጃን መሰረት ያደረገ የጤና መረጃ አሰባሰብ (DHIS2) ላይ የቅድመወሊድ ፣ወሊድ ፣ የክትባት አገልግሎት እንዲሁም የጤናው ዘርፍ አፈፃፀሙን መገምገም የማያስችል ጥናት የተከናውነ ሲሆን ይኸውም ወቅታዊ እና ታአሚኒ መረጃ በማመንጨት መረጃን መሰረት ያደረገ የጤና ዘርፍ ውሳኔ ሰጭነት ለማጎልበት የሚያግዙ ግብዓቶች በመድረኩ ተገኝተዋል፡፡
በአውደጥናቱም ላይ ከኢንስትዩቱ፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ ከክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች፣ ከዩኒቨርሲቲዎች አና አጋር አካላት የተወከሉ ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል።