የሸፈራው(ሞሪንጋ) ፈዋሽነት፡
June 28, 2023
የሸፈራው(ሞሪንጋ) ፈዋሽነት፡ ተአምረኛው ተክል! ትርክት ወይሰ እውነት? እስኮፒንግ ሪቪውን መሰረት ያደረገ ኢሹ ብሪፍ ላይ በመመስረት የጥናቱ ዉጤቶች ዙሪያ በኢንስቲትዩት የስልጠና ማዕከል የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእውቀት ትርጉምና ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ት ፊርማዬ ቦጋለ የምክክር መድረክ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ወቅት እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በቦታው ለተገኙት እንግዶች አስተላልፈዋል፡፡
በዉይይቱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ተመራማሪዎች፣ አካዳሚክ ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ሌሎች የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን የፖሊሲ ውይይትም ተካሂዷል፡፡
በቀረበው ሪፖርት ዙሪያ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቶባቸው ውይይቱ ተጠናቋል።