የባዮሲፍቲ ስልጠና እየተካሄደ ነው
June 1, 2021
የኢንስቲትዩቱ የብሔራዊ ላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የባዮ ሲፍቲና ባዮሴኪዩሪቲ ቡድን ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ያዘጋጀው አጠቃላይ የባዮሲፍቲ እና በኮቪድ 19 ላይ ያተኮረ ስልጠና በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ዶ/ር እዮብ አበራ የባዮ ሲፍቲና ባዮሴኪዩሪቲ ቡድን መሪ እና የስልጠናው አስተባባሪ እንደተናገሩት ስልጠናው የኢንስቲትዩቱ ስራተኞች በስራ ምክንያት ከሚከሰቱ የጤና አደጋዎች ለመታደግ፣ የኢንስቲትዩቱ ተገልጋዮችን እና ጎብኚዎችን ከተላላፊ በሽታዎች ለመከላከል እንዲሁም የኮቪድ 19 ጋር ተያያዥነት ካላቸው አገልግሎቶች ጋር ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና አደጋዎች በተጨማሪ በአጠቃላይ ማሕበረሰቡን እና አከባቢን በበሽታ አምጪ ተሃዋስያን መከላከል እና ቁጥጥር ማወቅ በማስፈለጉ የነዚህ ስልጠና አስፈላጊነት ገልጸዋል፡፡ በአጠቃላይ ስልጠናው የሚከተሉትን የባዮሴፍቲ ሁኔታዎችን ይዳስሳል፡-
- የስራ ላይ ደህንነት ጥንቃቄና ተግባራት
- በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በስራ ላይ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ
- የጸረ ተሃዋስያን ከሚካሎች አጠቃቀም
- የተበከሉ መሳሪያዎች እና አካባቢ አፀዳድ
- የሰውነት መከላከያ መሳሪያዎች አጠቃቀምና አወጋገድ
- አደገኛ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ
- የድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር
በስልጠናው ላይ 80 የኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች በሁለት ቡድን ተከፍለው እየተሳተፉ ሲሆን እንደ አስተባባሪዎቹ ይህ ሶስተኛ ዙር ስልጠና ሲሆን እስካሁን በአጠቃላይ 240 ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው የኮቪድ-19ን መመሪያን በተከተለ መልኩ በመከናወን ላይ የገኛል ፡፡