የብሄራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ከክልሎች ጋር መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
October 25, 2021
በኢትዮጵያ ያሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሄራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራ ትንተና ማዕከል ዳሬክቶሬት ከ 9 ክልሎች እና ከ 2 ከተማ መስተዳደሮች የተወጣጡ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት የጤና መረጃ ስርዓትን ለማሻሻል የሚደረግ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ በተመለከተ የጋራ የመግባብያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
የመግባብያ የስምምነት ሰነድ መፈራረሙ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ በክልሎች ያለውን የበሽታ ጫና በተመለከተ ጠንካራ መረጃ ለመለዋወጥ እና ለውሳኔ ሰጪነት የሚቀርብ ስርዓት ለመዘርጋት ና ለመሻሻል የተዘጋጀ መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል ።
የብሄራዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራ ትንተና ማዕከል ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር አለምነሽ ሀ/ማርያም የብሄራዊ የጤና መረጃ ስርዓት ና የክልል ጤና ቢሮዎች እንዲሁም የክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሚና ዙሪያ እና የዳሬክቶሬቱ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር አወቀ ምስጋናው በክልል ደረጃ ያለውን የበሽታ ምጣኔ ትንበያን ለማሻሻል በሚደረጉ የትብብር ስራዎች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን ለቀረቡት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተው የተዘጋጀውን የመግባብያ ሰነድ በመፈራረም ፕሮግራሙን አጠናቀዋል።