የብሔራዊ የወባ ቅኝት ጠቋሚ ጣቢያዎች ስራ መጀመር ላይ አውደ ጥናት በመካሄድ ላይ ነው
የኢንስቲትዩቱ የባክቲዮሮሎጂ፣ ፓራሲቶሎጂ እና የእንስሳት- ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ 25 ጤና ጣቢያዎች ማለትም የወባ ቅኝት ጠቋሚ ላይ የተቀናጀ የወባን ቅኝት ስራን ተግባራዊ ያደረገበትን አስመልክቶ የምርምር ስርፀት አውደ ጥናት ከሚያዝያ 12013 ዓ.ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ከጤና ሚኒስቴር ብሄራዊ የወባ ማስወገድ መሪ ሚኒስቴሩን ወክለው የተገኙ ሲሆን ከየክልሉ የጤና ጣቢያዎቹ ተወካዮችና ባለሞያዎችም እየተሳተፉ ይገኛል፡፡ በዐዉደ ጥናቱ የቅኝት ስራው ስኬቶችና ተግዳሮቶች እንዲሁም የስራውን ቀጣይነትና ጥራት በማስጠበቅ ለወባ ማስወገድ ያለውን ፋይዳ መሰረት ያደረገ ውይይት እንደሚካሄድ መርዐ-ግብሩ ያመላክታል፡፡ የተጠኑ ጥናቶች ላይ እና የአቅም ግንባታ ስራዎች፣ እስካሁን በተሰራው ስራዎች የተገኙ ውጤቶች እና ተግዳሮቶች፣ ጥቅም ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች እናም ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው ምን መደረግ እንዳላበት ከክልል የቅኝት ጣቢዎች እና ከጤና ሚኒስቴር የተወከሉ ባሉሙያዎች በተገኙበት ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ዶ/ር ገረመው ጣሰው የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ካሉት የጤና ስጋቶች አንዱ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የምጣነ ሀብት ተግዳሮት ጭምር መሆንን ገልፀው የሀገሪቱን ሶስት አራተኛ በሚሸፍኑ ቦታዎች መተላለፍ የሚችልና በነዚህ ቦታዎች ላይ ሰፍረው ያሉ የማህበረሰብ በግምት ከግማሽ በላይ ዜጎች ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰል፡፡ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ የወባ መቀነስ መመዝገብ በተመረጡ ቦታዎች የማስወገድ ስራ ማሳያ ተደርገው የሚወሰድና በሚቀጥሉ ዓመታት የወባ ማስወገድ ሥራው በሁሉም ወባማ ቦታዎች ተግባራዊ እንደሚሆን ተማላክተል፡፡ ሆኖም ግን ከአንድ ዓመት በፊት የተደራጀ የጤና ሚኒስቴር ዘገባ እንደሚያመለክተው ከአምስት ሚሊዮን በላይ ሰዎች የወባ ምርመራ ተካሂዶላቸው ወደ አንድሚሊዮን የሚጠጋ ሰዎች በሽታው ተገኝቶባቸው ተገቢውን ሕክም አገልገሎት ሲያገኙ ከ15 ሺህ በላይ ለወባ ተኝተው የታከሙ ሲሆን በሽታው የተባባሰ ደረጃ ላይ የደረሱና መቋቋም ያልቻሉ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን መረጃው ያሳያል ፡፡
የወባ ቅኝት ጠቋሚ ጣቢያዎች አስፈላገነትንና ዓላማን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ዋና አስተባባሪ ሲገልፁ የቅኝት ስራው የሚካሄደው የተለያዩ መልክዐ-ምድራዊ አቀማመጥ ካለቸውና የወባ ሥርጭት ያላቸው እንዲሁም የወረርሽ ታሪክና ስጋት ካለቸው 25 ጤና ጣቢያዎች ተመርጠው የወባ ተህዋስና ትንኝ ብግርነት የበሽታው ጫና የደረሰበትን ተዓማንነት ባለው መልኩ መረጃ የማመንጨትና ለወባ ማስወገድ ስራ የሚረዱ ሀገር አቀፍ ውሳኔ ለመስጠት የሚያበቃ መሰረተ-ሰፊ መረጃ ለጤና ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ለማቅረብ የሚውልይሆንል፡፡ በተጨማሪም የአየር ንብረት መለዋወጥን መረጃ በመከታተል ጣቢያዎቹ የወባ ወረርሽኝ ስጋት ቀድመው በመለየት የቅድመ- ዝግጅት እቅድ ማዘጋጀት ማስቻል ነው፡፡
የተጠቀሱትን መረጃዎች ለማመንጨት የሚያስችል የባለሞያ አቅምና ለጣቢያዎቹ የተለያዩ የግብዓት ማሟላት ስራዎች በስፋት ተከናውኗል፡፡ ከነዚህም የመረጃልውውጥን አሁናዊነት ለማረጋገጥና በቴክኖሎጂ ለመታገዝ የሞባይል መተግበሪያ ስራ ላይ ማዋል የተቻለ ሲሆን የመረጃ ጥራትን ለማረጋጥም ስልጠና ብቻ ሳይሆን በተፈለገ ጊዜ ድጋፍ የሚሰጡ የኢንስቲትዩቱ ባለሞያ በቂ ድጋፍ እደረገ ይገኛል፡፡
በስተመጨረሻም አጠቃላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ከላቦራቶሪ ግብአቶችና የባለሞያ የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲሁም የጥራት ቁጥጥር ስልትማስረፅ ትኩረት እንደሚገባው ከተሳታፊዎችና አስተባባሪዎች ግልፅና ሰፊ ውይይት ተካሂዶ ለወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይተው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ የቅኝት ስራ ወባን ከማስወገድ አንፃር ያለለው ሚና በጠቋሚ ጣቢያዎች እንደማሳያ ከፍተኛ ሚና የሚጠበቅ መሆኑንና ጤና ሚኒሰተርም አስፈላጊውን የሀብት ማሰባሰብና አቅርቦት ብቻ ሳይሆን የቴክኒካዊ ድጋፍ በመስጠት ክትትል እንደሚደረግ አቶ መብራህቶም ሀይሌ የጤና ጥበቃ የወባ ማስወገድ ፕሮግራም ሀላፊ በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የመረጃ ጥራትን ለማስጠበቅ የአቅም ክፍተት ያለባቸው ቦታዎችና የሙያ ዓይነቶች በተለይም የትንኝ ጥናትና ማይክሮስኮፕን በመጠቀም ለሚካሄደው የወባ ምርመራ አስመልክቶ ለባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ማካሄድ ወሣኝ መሆኑን ግንዛቤ ተይዟል፡፡ እንደመደመደሚያ የእንያንዳንዱ ጣቢያ አፈፃፀም በዋናነት በተለዩ መለክያዎች አንፃር ተገምግሞ ክፍተትን መለየት የሚሰጠውን ድጋፍ ከመለየትም አልፎ ተነሳሽነትን የሚያጎለብት መሆኑ ከስምምነት ላይ ተድርሷል፡፡