የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ ለኢንስቲትዩቱ የመኪና እርዳታ ሰጠ
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኢትዮÉያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ወርረሽኝ በሽታን ለመግታትና በህብረተሰብ ጤና ዙርያ ለሚያደረጉ ልዩ ልዩ ስራዎችን የሚያግዙ ተሽከርካሪ መኪናዎችን በእርዳታ አበረከተ፡፡
አቶ አስቻለው አባይነህ የኢትዮÉያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር በመኪናዎቹ ርክክብ ፕሮግራም ላይ ባደረጉት ንግግር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለኢትዮÉያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያደረገውን እርዳታ አመስግነው ከዚህ ቀደምም ተkሙ ለሀገሪቱ ጤና ሥርዓት መጠናከር በየጊዜው እያደረገ ያለውን ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘውም የተሸከርካሪዎች እጥረት በእለት ተእለት ስራዎች ላይ ልዩ ልዩ ተግዳሮቶችን እንደሚፈጥር ገልጸው የመኪናዎቹ በእርዳታ መገኘት ለተሽከርካሪ መኪናዎች ኪራይ የሚወጣውን ወÂዎችን በመቀነስና እየተሰሩ ያሉ የኮቪድ-19 ወረሽኝ ምላሽ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ብሎም እጅግ ሩቅ እና ተደራሽ ባልሆኑ ቦታዎች ሁሉ በመገኘት አስፈላጊውን የህብረተሰብ ጤና ድጋፍ ለማድረግ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ሚስተር ካርሎስ ሀዳዳስ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክስ ኮሚሽን የአስተዳደር ዳይሬክተር በበኩላቸው በህብረተሰብ ጤና ላይ እና የመጀመሪያ ደረጃ ስርአት ላይ መስራት ጠቀሜታው እጅግ የጎላ በመሆኑ ለእነዙህ ርእሰ ጉዳች ምንጊዜም ቢሆን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
ሚስተር ኡላሽ ዴሚሪንግ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮÉያ ተጠባባቂ ተጠሪ እና የአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ በኢትዮÉያ ኃላፊ በበኩላቸው የተባበሩት መንግስታት ልዩ ልዩ ተkማት የኮቪድ-19 ወርረሽኝ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን አውስተው ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም ወረሽኙን ለመከላከል እየተደረገ ያለው ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
በዚሁ ፕሮግራም መጀመሪያ ላይ እስከአሁን ድረስ በመላው አለም በኮቪድ-19 ወርረሽኝ የተነሳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና Òሎት ተደ¹ርል፡፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት በእርዳታ የተገኙት እነዚህ ሁለት ኒሳን ኮስተር መኪናዎች ከቀረጥ ነÑ ግምታቸው 3.6 ሚሊየን ብር የሚገመት መሆኑን ለማወቅ ተችላóል፡፡