የተፈናቀሉ አካላትን ምላሽ ሰጪ ባለሞያዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ የመጀመሪያ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ
November 29, 2021
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትዩት በህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል በህብረተሰብ ጤና አደጋ አመራር ስብዕዊ ዙሪያ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በጤና ዙሪያ ላይ የተሰማሩ ባለሞያዎችና በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ አካላትን ምላሽ ሰጪ ባለሞያዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ የመጀመሪያ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ።
የስልጠናው ዓላማም ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ማቋቋም እና በተለያዩ ምክንያቶች ለሚፈናቀሉ አካላት ለማቋቋም እንዲያስችል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑ እና በቀጣይም በ2ተኛ ዙር ለቀሩ ክልሎች ስልጠናው እንደሚስጥ ከመድረኩ ተገልፆ፤በተሰጠው ስልጠና ዙሪያ ሰፋ ያለ ሀሳብና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።
በተነሱ ሀሳቦች ዙሪያ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ሰጥተው በስልጠናው ለተሳተፉ አካላት የምስክር ወረቀት በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።