የአመራር ክህሎትን ስለማሳደግ ስልጠና ተሰጠ
July 12, 2021
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ከሴቶች ፎረም ጋር በጋራ በመሆን ለ22 የፎረሙ አባላት፣ ለ17አጋር ወንዶች፣ በድምሩ ለ36 ስዎች የሴቶችን የአመራርነት ክህሎት ስለ ማሳደግ፣ ስለ ልጆች አመጋገብና እድገት እንዲሁም ኮቪድ-19 በሴቶች ላይ እያደረስ ስላለው ተጽዕኖ በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ከቀን 02/11/13- 03/11/13 ዓ/ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የቆየ አምስተኛው ዙር ስልጠና በአዳማ ከተማ አካሄደ።
በስልጠናው የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የሴቶች እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር ወ/ሮ የሮም ሞረዳ እንደገለፁት ሰልጣኞቹ ከዚህ ስልጠና በኋላ ሰልጣኞቹ የልጆች አመጋገብና እድገት፣ልጆችን በአእምሮ በማጎልበት አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር በቂ ግንዛቤ የሚያገኙ ሲሆን እንዲሁም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ስራቸውን በሃላፊነት፣በታማኝነት እና በቅንነት በብቃት ማሸነፍ እንዲችሉና የራስ መተማመናቸው እንዲጨምር የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ጠቁመው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ እንደ ሀገር እንዲሁም በሴቶች ላይ እያሳደረ ያለው ተፅእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ይህንንም በመቀነስ እራሳቸውን ብሎም ከቤተሰባቸውን በተገቢው መልኩ መንከባከብ እንደሚገባ ግንዛቤ የሚወስዱበት ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።