የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የደብረማርቆስ ቅርንጫፍ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
March 13, 2023
በአለም ባንክ፣ በግሎባል ፈንድ እና በመንግስት የገንዘብ ድጋፍ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ባለሁለት ፎቅ ህንጻ Bio-Safety level-2(BSL-2) የሆኑ 28 ላቦራቶሪዎች እየተገነቡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በመጀመሪያው ዙር በግሎባል ፈንድ እና በመንግስት እየተገነቡ ካሉት 13 ላቦራቶሪዎች ውስጥ በአማራ ክልል በደብረማረቆስ ከተማ የአማራ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የደብረማረቆስ ቅርንጫፍ ግንባታው ተጠናቆ መጋቢት 1 ቀን 2015 ዓ/ም የተመረቀ ሲሆን፡ በምረቃ ስነስርዓቱም ላይ ኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የብሔራዊ ላቦራቶሪዎች አቅም ግንባታ ዳይሬክተር እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ፣ የደብረማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ፣የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት እና የአማራ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጀነራል በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ስራ ጀምሯል፡፡
በሁሉም ክልሎች በመገንባት ላይ ያሉት ቀሪ ላቦቶሪዎች ግንባታቸው ሲጠናቀቅ ጥራት ያለው የጤና ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግቱን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ይበልጥ ተደራሽ ከማድረጉ በተጨማሪም በተለያዩ ግዚያት የሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና ስጋቶችና አደጋዎችን አስቀድሞ በላቦራቶሪ የመለየት እና ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማሳደግ የጎላ ሚና ይኖራቸዋል፡፡