የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ኃላፊዎች ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ
February 2, 2024
የጤና ሚኒስቴር ተወካይ፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊዎች ጥር 23/2016 ዓ.ም ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በጤናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በመገጐብኘት ያለውን ግንኙነትን በተሻለ በማጠናከር የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው፡፡
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንስቲትዩቱ ከተሰጠው ኃላፊነት አንጻር አጠቃላይ እየሰራ የሚገኘውን ስራ ለልዑካኑ ገለጻ በማድረግ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከልዑካኑም የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው ተገቢውን ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከልን እና የተለያዩ የላቦራቶሪ የስራ ክፍሎች ልዑካኑ እንዲጎበኙ ያደረጉ ሲሆን በጉብኝቱ ወቅት የተመለከቱት የስራ እንቅስቃሴ እና ውጤት በሚገባ እንዳስደሰታቸው ልዑካኑ ተናግረዋል፡፡