የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ኢንስቲትዩቱን ጎበኘ
የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የኢንስቲትዩቱን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችና ምላሽ ማስተባበሪ ማዕከል ከኮቪድ ቫይረስ ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ያለውን የኢንስቲትዩቱ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለመገምገም ጉብኝት አደረገ፡፡
ቦርዱ የኢንስቲትዩቱን የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል የተለያዩ ቡድኖች ጉብኝት ያደረገ ሲሆን አቶ ዘውዱ አሰፋ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪ ማዕከል ምክትል ሃላፊ የቡድኖቹ አደረጃጀትና አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በዝርዝር ለቦርዱ አባላት ገለጻ አድርገዋል፡፡
ከቦርዱ አባላት ጋር ስለቫይረሱ ወረርሽኝ የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች ምን እንደሚመስሉ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ዶ/ር ኤባ አባተ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር በሽታው በሃገራችን ከመከሰቱ በፊት የነበሩትን የቅድመ ጥንቃቄ እና በሽታው ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተሰሩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎችን እንዲሁም አጠቃላይ አለም አቀፍ መረጃዎችን ጭምር በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
ላቦራቶሪን አስመልክቶም በመጀመሪያ በ24 ሰዓት በሃገር ደረጃ መመርመር የሚቻለው 33 ናሙናዎችን ብቻ እንደነበረና በአሁኑ ሰዓት 8 ሺ ናሙናዎችን መመርመር መቻሉንና በቀጣይ በ24 ሰዓት ውስጥ 14 ሺ ናሙናዎችን መመርመር እንዲቻል ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት የተለያዩ ጥያቄዎች ከቦርዱ አባላት የተነሱ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሰፊ ማብርሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም ከተለያዩ ሴክተር መስሪያቤቶች ጋር ያለው ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ የሚታዩት የተለያዩ የግብአት ክፍተቶች ከሚመለከተው አካላት ጋር በመወያየት መፍታት እንደሚገባ ፣ ለሕብረተሰቡ የሚሰጡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸው፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት ቤት ለቤት የምርመራ ስራ መካሄድ እንዳለባቸው የሚሉና ሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡