የአደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ባለሙያዎች ከመጋቢት 7 – 10/2014ዓ.ም በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል ።

March 28, 2022
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበርያ እና የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ዙሪያ ለክልል ጤና ቢሮዎች/ጤና ኢንስቲትዩቶች፣ ለዞን ጤና መምሪያዎች፣ ለሀገር መከላከያ ጤና መምሪያ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና መምሪያ እንዲሁም ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ባለሙያዎች ከመጋቢት 7 – 10/2014ዓ.ም በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል ።
ስልጠናው የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በፍጥነት ለመቆጣጠር በሕህብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበርያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) እና የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ላይ ግንዛቤን በማሳደግ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ባለሙያዎች መረጃን እና ሀብቶችን በብቃት እንዲያቀናጁ የሚያግዝ ነው።
በስልጠናውም የቅድመ ማስጠንቀቅያና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ አሰፋ የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን በብቃት ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት አበርክተዋል።የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበርያ እና የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ዙሪያ ለክልል ጤና ቢሮዎች/ጤና ኢንስቲትዩቶች፣ ለዞን ጤና መምሪያዎች፣ ለሀገር መከላከያ ጤና መምሪያ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጤና መምሪያ እንዲሁም ለጅማ ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል ባለሙያዎች ከመጋቢት 7 – 10/2014ዓ.ም በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰቷል ።
ስልጠናው የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎችን በፍጥነት ለመቆጣጠር በሕህብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበርያ ማዕከል (Public Health Emergency Operation Center) እና የክስተት አስተዳደር ስርዓት (IMS) ላይ ግንዛቤን በማሳደግ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ባለሙያዎች መረጃን እና ሀብቶችን በብቃት እንዲያቀናጁ የሚያግዝ ነው።
በስልጠናውም የቅድመ ማስጠንቀቅያና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዘውዱ አሰፋ የመዝጊያ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን በብቃት ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት አበርክተዋል።