የኢትዮጲያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ስነ -ምግብ ምርምር ዳሬክቶሬት ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን “leveraging systems approach of Healthier and Sustainable Diet Policy in Ethiopia” ፕሮጀክት ማሰጀመሪያ አውደ ጥናት
የኢትዮጲያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ስነ -ምግብ ምርምር ዳሬክቶሬት ከፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ በመሆን “leveraging systems approach of Healthier and Sustainable Diet Policy in Ethiopia” ፕሮጀክት ማሰጀመሪያ አውደ ጥናት በቀን 25/12/13ዓ/ም በስካይላይት ሆቴል የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ፡፡
የአውደ ጥናቱ ዋነኛ አላማም በኢትዮጲያ ውስጥ ያለው የምግብ ስርዓት ጤናማ ያልሆነ ምግብ ለዝቅተኛ ገቢ እና ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች የመከላከል እና ጤናማ ምግቦችን ለማቅረብ የሚደግፍበትን ደረጃ መተንተን እና የፖሊሲው አቅጣጫ መጠቆም መሆኑ ከመድረኩ ተገልጿል፡፡
በዋናነት ጥናቱ ትኩረት የሚያደርገው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች በተለይም ለሴቶች እና ለህጻናት የአመጋገብ ሁኔታ እና ችግሮችን የሚገልጽ የአመጋገብ ዘይቤ እና ክፍተቶች እንደሚያጠና፣ በኢትዮጲያ ውስጥ ለጤናማ አመጋገብ አሁን ያለውን ፖሊሲ(የፊስካል፣ የቁጥጥር እና ሌሎች ጣልቃ ገብነቶችን) እና የተለያዩ ተዋንያን እና በምግብ ስርዓቱ ውስጥ ያላቸውን ሚና ለመገምገም ያለመ የተቋማዊ ትንተና እንደሚያደርግ፣ በተለይም የምግብ ምርት ንዑስ ስርዓት ላይ በማተኮር በተለይም የምግብ መጠን፣ ብዙሃነት እና የተመረተ የምግብ ወቅታዊነት መጓጓዝ በተጨማሪም የምግብ ምርቶችን ሰንሰለት ለገበያ ማቅረብ እና የምግቦቹ ባለድርሻ አካላት ሚና ትስስርን እንደሚያጠና ተመላክቷል፡፡
ይህንንም ጥናት ለማካሄድ 3አመታትን እንደሚፈጅ እና የሚያስተባብሩ አካላትም የኢትዮጲያ ፖሊሲ ምርምር ጥናት ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጲያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መሆናቸው ተጠቅሶ፤ ለጥናቱ የቴክኒክ ድጋፍ ከካናዳ megill university እና በኔዘር ላንድ wagenigen university እንደሚደረግ ጥናቱ በሚካሄድበት ወቅትም ለሚያስፈልገው ገንዘብ አንድ ሚሊየን የካናዳ ዶላር የካናዳ የልማት ድርጅት ድጋፍ
እንደሚያደርግ እንዲሁም ጥናቱን በዋናነት የሚያስተባብሩት አካላትም ዶክተር አለበል ባይሩ እና ዶክተር ማስረሻ ተሰማ መሆናቸው ተገልጿል፡፡