የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ቤንሽ.አ.ኢ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የሕብረተሰብ ጤና ምርምርን ለማሻሻል የሚያስችል የ3 አመት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።
ኢትዮጵያ/ ስፔን /ጥር 2 2014 የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (ኢ.ሕ.ጤ.ኢ) እና መሰረቱን ስፔን ያደረገው ቤንሺ.ኤ.ኣይ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስንና ማሽን ለርኒንግ በመጠቀም የህብረተሰብ ጤና ምርምሮችን ለማገዝ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ምርምር ስራና ውጤቶችን በዘመናዊ እውቀቶች ለማገዝ ያለመ ሲሆን ለ3 ዓመት የሚቆይ ነው፡፡
ዘመናዊ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በምግብ እና ስነ ምግብ ምርምሮች ላይ ለመተግበር ዝግጅት ሲደረግ የመጀመሪያ ጊዜ ነው። የኢ.ሕ.ጤ.ኢ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና አሰራሮችን በመጠቀም መረጃን መሰረት ያደረገ ምርምር፡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እንዲሁም ስትራቴጂዎችን በማጐልበት የሕብረተሰብ ጤናን ለማሻሻል የሚያስችለው ስምምነት ሲሆን በቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ለትርፍ ያልተቋቋመው ቤንሺ.ኤ.ኣይ ከተሰኘ ተቋም ጋር በጋራ የሚሰራ ነው፡፡
መግባቢያ ሰነዱ የሚከተሉትን ሠፊ የትብብር ስራዎች ያጠቃልላል፡፡
- ለአትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፡ በመጀመሪያ ምዕራፍ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስና ማሽን ለርኒንግ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለኢ.ሕ.ጤ.ኢ አስተዳደር፣ ከ50 በላይ ለሚሆኑ ተመራማሪዎችና የጤና ባለሙያዎች በቤንሺ.ኤ.ኣይ አማካኝነት ይሰጣል፡፡
- በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሳሪያዎች የታገዘ ምርምር መስራትና መረጃን የማጠናከር ስራ በተመረጡ የማሕበረሰብ የአመጋገብ ስርዓቶች ላይ ይከናወናል፡፡
- በኢትዮጵያ ጥራታቸውን የጠበቁ የስነ-ምግብ ምርምሮችን ለመስራት በትብብሩ ወቅት የተሰሩ ውጤቶችን ይፋ ማድረግና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን እንዲጠቀሙ ማበረታታትን ያጠቃልላል፡፡
የኢ.ሕ.ጤ.ኢ የምግብ ሳይንስና እና የስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት ከቤንሺ.ኤ.ኣይ ጋር አብሮ በመሆን ይህን ስራ ይመራል፡፡ በዋናነትም በአመጋገብ ችግሮችና የምግብ እጥረትን መሰረት ያደረጉ የምርምር ስራዎች ይሰራሉ፡፡መግባቢያ ሰነዱ በተፈረመበት ወቅት የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ማስረሻ ተሰማ እንደተናገሩት “የኢ.ሕ.ጤ.ኢ ከቤንሺ.ኤ.ኣይ ጋር አብሮ መስራቱ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግን በመጠቀም የስነ ምግብ የምርምር ስራዎችን ለማሳደግ ትልቅ ሚና አለው። በተጨማሪም የስነ-ምግብ ምርምር ተመራማሪዎች የማሽን ለርኒንግ እና አርቴፍሽያል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የምርምር ውጤቶችን እንዲያዘጋጁ ያግዛቸዋል።”
የቤንሺ.ኤ.ኣይ. መስራች እና ዋና ዳሬክተር የሆኑት ዶ/ር አፍሪካ ፔሬንዝ በበኩላቸው “ከኢ.ሕ.ጤ.ኢ ጋር አብረን የመስራት ትልቅ እድል በማግኘታችን እጅግ ደስተኞች ነን፡፡ ከመንግስት ተቋሞች ጋር አብረን መስራታችን ዓለምአቀፍ የጤና ግቦችን በማሻሻል ረገድ ቁልፍ ሚና አለው፡፡ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሞያዎቻችን ከኢ.ሕ.ጤ.ኢ ተመራማሪዎች የሚያገኙትን ተጨባጭ እውቀት ከዘመናዊው እውቀት ጋር በማቀናጀት ለዜጎች ለማህበረሰቡ እንዲሁም በሕብረተሰብ ጤና ዙሪያ ላይ መረጃን መሰረት ያደረጉ አዳዲስ መረጃዎችን ወደፊት ለማምጣት በጋራ እንሰራለን።”
በኢ.ሕ.ጤ.ኢ እና ቤንሺ.ኤ.ኣይ. የተደረገው ስምምነት ከ2022 እስከ 2024 የሚዘልቅ ይሆናል።
ለመገናኛ ብዙሃን እና ሌሎች ጥያቄዎች ካላችሁ ከታች የተጠቀሱትን አድራሻ በመጠቀም ምላሽ ማግኘት ይቻላል፡፡
ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የምግብ ሳይንስና እና ስነ ምግብ ምርምር ዳይሬክቶሬት
ሀሲና ኡስማን (የኮሚኒኬሽን ባለሞያ)
ቤዛ ተሾመ (ዳታ ማናጀር)
Hassina.nipn@gmail.com/beza,nipn@gmail.com
—————————————————————————
ቤንሺ.ኤ.ኣይ
ሱሚኮ ታናካ ፑሽ፣
አለምአቀፍ የአጋርነት መሪ
sumiko@benshi.ai