የኢትዮጵያ የሕብረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተጓዦችና ድንበር ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም.
February 10, 2023
የኢትዮጵያ የሕብረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተጓዦችና ድንበር ጤና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ.ም. ግማሽ አመት ዕቅድ አፈፃፀም በቦሌ አለም አቀፍ አወሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ካሉት ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡
ውይይቱ በአወሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ለሚደርጉት የድንበር ተሻጋሪ የተላላፊ በሽታ ቁጥጥር የባለድርሻ አካለትን ተሳትፎና አጋርነት ለማጠናከር ያለመ ነው፡፡ በምክክር መድረኩ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት፤ ከኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት፣ከጉምሩክ ኮሚሽን አቬሽን ባለስልጣን ፣ ከኢትዩጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ የምግብና መድሐኒት ቁጥጥር አሰተዳደር፣ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከአቬሽን ሴኩሪቲ፣ ከአዲሰ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ከተማ መሰተዳደር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል ናቸው፡፡