የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የ2015 ዓ.ም የትንሳዔ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት
April 13, 2023
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳዔ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ፤
ኢንስቲትዩቱ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የመከላከል እና መቆጣጠር ስራዎች፤ የጤና ላብራቶሪዎች አቅም ግንባታ እና የማጣቀሻ ምርመራዎች፤ የሕብረተሰብ ጤናና ሥርዓተ-ምግብ ችግሮች፣ ፕሮግራሞችና ስትራቴጂዎች ምርምር፤ እንዲሁም የጤናና ጤና ነክ መረጃዎች ቅመራና ትንተና ስራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ አንጋፋ ተቋም መሆኑን ሲገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
ሕብረተሰቡ የትንሳዔ በዓልን ሲያከብር ከወረርሽኞች እና ሌሎች የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉ መልዕክታቸውን እንደሚከተለው ያስተላልፋሉ፦
- የኮቪድ_19 በሽታ ምልክቶችን ያሳዬ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና እንዲያገኝ፤
- የኮቪድ_19 ክትባትን በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ እንዲከተቡ፤
- የግልና የአካባቢ ንፅህናን በመጠበቅ ከተላላፊ በሽታዎች እራስዎንና ቤተሰብዎን እንዲከላከሉ፤
- ምግብን አብስለው ወይም በአግባቡ አጥበው በመጠቀም ከተላላፊ በሽታዎች እራስዎንና ቤተሰብዎን እንዲጠብቁ፤
- ጤንነታቸው ያልተረጋገጠ የእንስሳት ተዋፅዖ ባለመመገብ ከእንስሳት ወደ ሰው ከሚተላለፉ በሽታዎች እራስዎንና ቤተሰብዎን እንዲጠብቁ፤
- ማንኛውም ድንገተኛ የሆነ የጤና ችግር ለምሳሌ አጣዳፊ ተቅማጥ ወይም ትውከት ካጋጠመዎ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ ህክምና አንዲያገኙ፣ እንዲሁም ወደ 8335 በነፃ በመደወል ሪፖርት እንዲያደርጉ፤
- ትንኝ ሊራባበት የሚችል ውሃ ያቆረ ጉድጓድ እና የተጣለ የቤት ዕቃ በማስወገድ እና አጎበርን በአግባቡ በመጠቀም የወባ በሽታን እንዲከላከሉ፤
- ማንኛውንም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ወይም ወረርሽኝ ጋር የተያያዘ ጥቆማ ለመስጠትና መረጃ ለማግኘት ወደ 8335 እንዲደውሉ፤
- በድርቅ፣ በጎርፍ፣ በግጭት እና በመሳሰሉት ምክኒያቶች ከቤታቸው እና ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖችን በማሰብና ያለውን በማካፈል ተደጋግፈው በዓሉን እንዲያከብሩ፤ በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
መልካም በዓል!
ዶ/ር መሳይ ኃይሉ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር