የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስርዓተ ጾታ ማካተቻ ማኑዋል እና ተያያዥ መመሪያዎችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ በኪሎሊ ሆቴል ከመጋቢት 29-30/2014 ተካሄደ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የስርዓተ ጾታ ማካተቻ ማኑዋል እና ተያያዥ መመሪያዎችን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ በኪሎሊ ሆቴል ከመጋቢት 29-30/2014 ተካሄደ፡፡
በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የመርሃ ግብሩ መዘጋጀት ዋና አላማ በሁሉም ዘርፉ የማህበረሰቡ ግማሽ አካል የሆኑትን ሴቶችን በእኩልነት ሳያሳትፍ እና ሴቶችን ሳያበቃ ሊሳካ ስለማይችል፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ቅድሚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሃገሪቱ ዙሪያ የሚገጥማቸውን የሥርዓተ ፆታ እኩልነት እጦትና መድልዎን መታገል የኢንስቲትዩታችን በሁሉም የስራ ክፍሎች እና ዘርፎች ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ በማካተት በቀጣይ ጊዜ በሁሉም የስራ ክፍሎች ላይ የስርዓተ ጾታ ጉዳይን በማካተት እና ተግባራትን በሚፈጸሙበት ወቅት Gender sensitive አድርጎ በመስራት በኩል የሚጠበቀውን ሃላፊነት ለመወጣት እንዲያስችል ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ማርታ አበራ እንደገለፁት አጠቃላይ የማኔጅመት አባላት ይህንን ስልጠና ሲወስዱ በኢንስቲትዩቱ በሁሉም ዙሪያ የሚስሩ ስራዎች ላይ የስርዓተ-ፆታ ጉዳይ ትኩረት ተሰጥቶት እንዲሰራ ሲሉ ገልፀው አክለውም ሴቶች በጤናው ዘርፍ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳ ስልጠና መሆኑን በተጨማሪም ደግሞ ስልጠናው አጠቃላይ እንደ ማህበረሰብና በግል ህይወታችን ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርዓት የሚያግዝ ስልጠና ነው ሲሉ ገልፀዋል።
በመድረኩም በአገር አቀፍ የጤናው ዘርፍ የስርዓተ ጾታ ማካተቻ ማኑዋል የጤናው ዘርፍ የሴ/ህ/ወ/ጉ የ5ዓመት ስትራቴጂ እቅድ ከ WHO የመጡት ፕሮግራም ማኔጅመንት ኦፊሰር የሆኑት ዶ/ር ፍቅር መለሰ እንዲሁም የስራ ቦታ ላይ ጾታ ጥቃት መከላከያ ምላሽ አሰጣጥ መመሪያን ዙሪያ አቶ አቤል ሞሴ ከጤና ሚኒስቴር የጠናት ጽሁፍ አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል፤ በተጨማሪም ምግብን መሰረት ያደረገ መመሪያ ዙሪያ ከኢንስቲእዩቱ የተገኙት አቶ ዳዊት አለማየሁ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡