የኢንስቲትዩቱ መሪ ተመራማሪ የሕየወት ዘመን የላቀ ሽልማት ተሸለሙ
October 15, 2019
የኢንስቲትዩቱ መሪ ተመራማሪ አቶ አበበ በቀለ በ21ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ ላይ የሕይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ በመሆናቸው ኢንስቲትዩቱ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ይገልጻል፡፡
አቶ አበበ በቀለ በ1976 ዓ.ም በምግብ ባለሙያነት በኢትዮጵያ የምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት በአሁኑ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነው ስራ የጀመሩት፡፡ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን Health Service Research ኔዘርላንድስ ከሚገኘው ኢራስመን የሕክምና ት/ቤት አግኝተዋል፡፡ በቀድሞው የምግብ ጥናት ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ጥናት ምርምር የስልጠና ቡድን ሃላፊ፣ አፕላይድ ኮሚኒቲ ኒውትሪሽን ም/ ሃላፊ፣ ኤፒዴሞሎጂ እና ፐብሊክ ሄልዝ ሊደር በመሆን አገልግለዋል፡፡
ከ19 በላይ የምርምር ስራዎች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አራቱ በሳቸው የተመሩ ናቸው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶችን እንደ SARA, SPA, EMoC, STEP Surveillance on NCD እና Mini DHS የመሳሰሉትን አስተባብረው መርተዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በመሪ ተመራማሪነት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥነ ጤና እና ሥነ ተዋልዶ ዳይርክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡