የኢንስቲትዩቱ ብሔራዊ የጤና ላቦራቶሪ ሥርዓት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ አዲስ የተዘጋጀውን የብሔራዊ የጤና ላቦራቶሪ ስትራቴጂክ ዕቅድ
የኢንስቲትዩቱ ብሔራዊ የጤና ላቦራቶሪ ሥርዓት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ አዲስ የተዘጋጀውን የብሔራዊ የጤና ላቦራቶሪ ስትራቴጂክ ዕቅድ ዙሪያ ከየካቲት 24-25 ቀን 2015 የክልል ጤና ኢንስቲትዩቶች እና ክልል ላቦራቶዎች ፣ አጋር ድርጅቶች፣ የላቦራቶሪ፣ የሙያ ማህበራት፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የምክክር አውደ ጥናት በአዳማ ከተማ አካሄደ።
በዕለቱም የብሔራዊ የላብራቶሪዎች አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳንኤል መለሰ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ጥሪ የተደረገላችዉን እንግዶች በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት ስም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግራቸዉን በመጀመር ዛሬ በዚህ ወርክሾፕ የተገናኛንበት ዋና አላማ የቀጣይ የ5 አመት ብሔራዊ የጤና የላብራቶሪ እስትራቴጂክ ፕላን በድራፍት ደረጃ በተዘጋጀው ዶክሜንት ላይ ሁሉም የባለ ድርሻ አካላት የተዘጋጀዉን ዶክሜንት ማበልጸግና ጥቅም ላይ ማዋል የወርክሾፕ ዋና አላማ መሆኑን ገልፀዋል።
አክለውም እንደሚታወቀዉ በኢትዮጵያ ላብራቶሪዎች ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ብዙ ጠንካራ የሚባሉ ስራዎች መሰራታቸዉን አዉስተዉ ከነዚህ ዉስጥ የላብራቶሪ ግንባታ እንዲሁም የክልል ላብራቶሪዎች የተለያዩ ላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎቶችን ማስፋፋት እና የተለያዩ የላብራቶሪ አቅም ግንባታ ስራዎችን ከማከናወን አንፃር ብዙ አበረታች ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰው፤ በተለይ ላለፉት ሶስት አመታት ከድንገተኛ አደጋዎች ጋር በተያያዘ ላብራቶሪዎች ቁልፍ ሚና እንደነበራቸዉ ለመገንዘብ መቻሉን ጠቁመው በተዘጋጀዉ ድራፍት እስትራቴጂክ ፕላን ዉስጥ የሁላችሁም እገዛ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፡፡ በቴክኒክ ቡድን ውስጥ ስራውን እያገዙ ያሉ አካላትን በኢንስትትዩቱ ስም አመስግነዋል።
በመድረኩም የላብራቶሪ ጥራት ማሻሻያ እና እውቅና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ አቻምየለህ ሙሉጌታ የስትራቴጂክ እቅድ አጠቃላይ እይታ እና የስትራቴጂክ እቅዱ ማዕቀፍ እና ይዘቶች ዙሪያ ፕረዘንቴሽን አቅርበዋል።