የኢንስቲትዩቱ የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሄደ
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ፣ ም/ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የኢንስቲትዩቱ አመራር አባላት፣ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኃላፊዎች እና የጤና ልማት አጋሮች በተገኙበት በቢሾፍቱ ከተማ ከነሐሴ 18/2015 ዓ.ም ጀምሮ ተካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ መልካም አፈፃፀሞችን የምንገመግምበትና የጋራ የምናደርግበት ፈተናዎቻችንን መተንተንና አዳዲስ መፍትሔዎችን በማስቀመጥ ለጀመርነው በጀት ዓመት የሕብረተሰብ ጤና እቅድ በግብዓትነት የምንጠቀምበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በግምገማ መድረኩም የኢንስቲትዩቱ አመታዊ እቅድ አፈጻጸም፣ ወቅታዊ የወረርሽኝ ዝግጁነት እና ምላሽ ተግባራት፣ የሁለተኛው የኢትዮጵያ አገልግሎት አሰጣጥ ጥናት ግኝቶች፣ የምግብ እና ስነ-ምግብ ስትራቴጂ መነሻ ዳሰሳ ጥናት ግኝቶች እና አንዳንድ የክልል የሕብረተሰብ ጤና ተቋማት አፈፃፀሞች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
The Institute’s plan Annual Review Meeting was held
The Ethiopian Public Health Institute’s (EPHI) 2015 fiscal year Annual Review Meeting was held in Bischoftu town on August 18/2015 in the presence of the EPHI’s Director General Dr. Mesay Hailu and Deputy Director General Dr. Getechew Tolera, EPHI’s management members, representatives from the Ministry of Health, heads of regional Public Health Institutes, and partner oganizations.
During the opening ceremony of the review meeting, Dr. Mesay Hailu stated that the main objective of the meeting is to evaluate and share important achievements, analyze our challenges and explore new solutions that will be used for the annual public health planning.
In the review meeting the Institute’s indicator based annual plan achievements and performances; the current ongoing outbreaks preparedness and responses activities, the Second Ethiopian Service Provision Assessment (ESPA) findings; the Food and Nutrition Strategy Baseline Survey Findings and regional public health institutes performances were presented.
Finally the Director General and Deputy Director General addressed issues raised by the participants and explained and gave directions for the ways forward