የኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች ጷጉሜን 1 የሚውለውን የአገልጋይነት ቀንን አስመልክቶ ወይይት አደረጉ

September 6, 2023
የኢንስቲትዩቱ ዋና ደይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት አጠቃላይ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ባለፈው አመት የተከሰቱ የተፈጥሮ እና ሰው ስራሽ ችግሮችን ተከትለው የተፈጠሩ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመቆጣጠርና ለመከላከል በፍፁም ቁርጠኝነትና የአገልጋይነት ስሜት ሕብረተሰቡን ማገልገላቸውን ገልፀው ካመሰገኑ በኋላ በቀጣይም ይህንኑ በሁሉም መልኩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ይልማ በቀh የኢንስቲትዩቱ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ደይሬክተር ጷጉሜን 1 የአገልጋይነትን ቀንን በማስመልከት በፌድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተዘጋጀዉን ሰነድ አቅርበዋል።
የቀረበውን ሰነድ መሠረት በማድረግም በኢንስቲትዩቱ ም/ል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ አወያይነት የኢንስቲትዩቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በታዩ ችግሮችና የመፍትሔ ሐሳቦች ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል።