የእብድ ወሻ በሽታ (Rabies) የላብራቶሪ አገልግሎት ላይ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና እና ግምገማ ተጠናቀቀ
December 4, 2023
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት በእብድ ውሻ በሽታ የላቦራቶሪ አገልግሎት ዙሪያ ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ ከዘርፉ ባለሙያዎችና ዳይሬክተሮች ከህዳር 17/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሰጥ የነበረውን በስራ ላይ ስልጠና እና ግምገማ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ።
ዶ/ር ይመር ሙሉጌታ የኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣ ፓራሳይቲክ እና እንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ተመራማሪ እንደገለጹት ስልጠናው ከትግራይ፣ ከአማራና ከሱማሌ ክልል ለመጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡
“ኢንስቲትዩታችን ከአለም የጤና ድርጅት እንዲሁም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የእብድ ውሻ በሽታን በመቆጣጠርና መከላከል ዙሪያ ላለፉት አመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ውስጥ በላቦራቶሪ የተደገፈ የእብድ ውሻ በሽታ ቅኝት በተስፋፋባቸው ክልሎች በተለይ በCDC ድጋፍ የላቦራቶሪ ማስፋፊያ እና ቁጥጥር አገልሎት በአብነት ይጠቀሳል፣” በማለት ዶ/ር ይመር አብራርተዋል።