የእናቶች ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓት ግምገማ ውጤት ማሳወቂያ መድረክ የተለያዮ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት አዲስ አበባ አምባሳደር ሆቴል ተካሄደ

April 1, 2022
የእናቶች ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓት ግምገማ ውጤት ማሳወቂያ መድረክ የተለያዮ ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት አዲስ አበባ አምባሳደር ሆቴል ተካሄደ።
በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክር አቶ አስቻለዉ አባይነህ የመግቢያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸዉም ኢንስቲትዩቱ ከጤና ሚኒስቴር እና ከ አጋሮቹ ጋር በመተባበር ላለፉት 9 አመታት ሲሰራ ወደነበረዉ የእናቶች ሞት ቅኝት እና ምላሽ ስርአት ግምገማ ዲሰሚኔሽን አዉደጥናት ላይ እንኳን በሰላም መጣችሁ መልክታቸዉን አስቀድመዉ
የግምገማው ዓላማም የእናቶች ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓቱ ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር ክፍተቱን ለማወቅ እና ለማሻሻል ሲሆን የዚህም ግምገማ ቁልፍ ግኝቶች የእናቶች ሞት ቅኝት እና ምላሽ ስርዓት በሀገሪቱ ያለውን ቅልጥፍና እና ውጤታማነት ለማሻሻልና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር አብሮ መስራት መሆኑን ተናግረዋል።
ሃገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት አስርተ አመታት የእናቶችን ጤና ከማሻሻል ባሻገር አመርቂ ዉጤቶችን ማስመዝገብ መቻሏን እና የሚፈለገዉ ዉጤት ቢመዘግብም አሁንም የእናቶች ሞት በሁሉም ቦታዎች እየተመዘገበ መሆኑን ጠቁመዉ የእናቶች ሞት መንስኤዎች ብዙ ቢሆኑም ቤት ዉስጥ መዉለድ፣ ዉስን የጤና አገልግሎት ሽፋን እና የማዋለጃ ግብአቶች እንዲሁም ዉስን የሰለጠነ የሰዉ ሃይል እንደዋና ዋና ምክንያቶች መጥቀስ እንደሚቻል ገልጸዋል።
አክለዉም በቅኝቱም መሰረት የምላሽ ስራዎችን በመስጠት ተመሳሳይ የእናቶችን ሞት ከመቀነስ አንጻር አመርቂ ዉጤት ቢመዘግብም በሀገራችን በዓመት ከ13,000 በላይ የእናቶች ሞት የሚጠበቅ ቢሆንም ሪፖርት የሚደረገው ከ9.5 በመቶ የማይበልጥ መሆኑን ጠቅሰዉ እነዚህ ችግሮች በግምገማዉ ሪፖርት በጥልቀት እና በስፋት የተዳሰሱ ሲሆን በዚህም አዉደጥናት ዉጤቱን መሰረት በማድረግ ዋና እስትራቴጂክ እቅድ እና ዝርዝር አቅድ እንዲዘጋጅ አሳስበዉ መድረኩን በይፋ ከፍተዋል።
በመድረኩም የእናቶች ሞት ቅኝት ምላሽ ስርዓት አተገባበርን በተመለከተ የተሰራ ሀገር አቀፍ ጥናት ውጤት እና የእናቶችና ጨቅላ ህፃናት ሞት ቅኝትና ምላሽ ስርዓት ትግበራ ያጋጠመው ተግዳሮት እና ስርዓቱን የተሻለ ለማድረግና የመወያያ ነጥቦች ቀርበዋል ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።