የኮሌራ መቆጣጠሪያ እቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ
December 27, 2022
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሃገር አቀፍ ደረጃ ኮሌራን ለመቆጣጠር በተዘጋጀው እቅድ አተገባበር ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲጋሞ የህብረተሰብ ጤና ኢስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ኃይሉና ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ፣ የክልል ጤና ቢሮና የህበረተሰብ ጤና ኢስቲቲዩት ከፍተኛ ኃላፊዎች እንዲሁም የተለያዩ አጋር ድርጅት ኃላፊዎች በተገኙበት ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ሂልተን ሆቴል የምክክርና አተገባበር ዙሪያ አውደ ጥናት ተካሄደ፡፡
የአዋደ ጥናቱ ዋና ኣላማ የኮሌራ መቆጣጠሪያ ዕቅድን በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ኮለራ በሽታ በሃገራችን ላይ የሚያስከትለውን የጤና ጉዳት ለመቀነስ ታሳቢ በማድረግ የሰዎችን የሞት መጠን በ90% በመቀነስ የህብርተሰቡን ጤና ለማስጠበቅ ነው።