የኮሌራ መቆጣጠሪያ እቅድ አተገባበር ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
ታህሳስ 17 2015 ዓ.ም
የኮሌራ በሽታ ወራርሽኝ በኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ሲከሰት መቆየቱ የሚታዋቅ ነዉ። በአሁኑ ወቅት ወራርሽኙ ከነሐሴ 21 2014ዓ.ም ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል ሶስት ዞኖች (ባሌ፤ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ) ውስጥ በሚገኙ 9 ወረዳዎች (ሀረናቡሉክ፣ ዶሎመና፣ በርበሬ፣ መዳወላቡ፣ ጉራዳሞሌ፣ ቀርሳዱላ፣ ጉራዳሞሌ፣ ግርጃና ጎሮ)፤ እንዲሁም በሶማሌ ክልል ሊበን ዞን በሚገኙ 2 ወረዳዎች (ከርሳዱላና ጉራዳሞሌ) ወረርሽኙ ተክስቶባቸዋል፡፡ ወረርሽኙ ከጀመረ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 16 2015ዓ.ም በአጠቃላይ 738 ሰዎች ህምም(539 ሰዎች ከኦሮሚያ 199 ሰዎች ከሶማሊ ክልል) ና ለ25 ሰዎች ሞት (15 ሰዎች ከሶማሊ 10 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል )ምክንት ሆኗል፡፡ በአጠቃላይ በወርሽኙ 3.4% የሞት ምጣኔ በመቶኛ ተመዝግቧል፡፡
ለወረርሽኙ ለማከም የሚያስችሉ 13 ግዜያዊ የኮሌራ ማከሚያ ማእከላት የተዘጋጁ ሲሆን በተጨማሪም የህክምና ግብአቶች፡ለማዕከላቱ ተሰራጭቷል፡፡ የወረርሽኙን ምላሽ ለማጠናከር በተለያየ ግዜያት ሁለት ግዜ የተለያዩ የሙያ ስብጥር ያላቸው የፈጥኖ ደራሽ ምላሽ ሸጪ ቡድን ወረርሽኙ በተከሰተባቸው ቦታዎች በመላክ ድጋፍ ተደርጎል፡፡
በተደጋጋሚ ሚከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመቀነስ የሚስችል ስር ነቀል ስራ ለመስራት ያስችል ዘንድ ባለድረሻ አካላትን ያሰተፈ የተለያዩ አጋርድርጅቶች ጋር በመሆን የስምንት አመት የኮሌራ መቆጣጠሪያ/ማጥፊያ ሰነድ ተዘጋጅቶል፡፡ ይህ ዕቅድ በኮሌራ ምክንያት የሚከሰተውን የሞት ምጣኔ 90 በመቶ ለመቀነስ ያለመ ሲሆን በተደጋጋሚ የሚከሰትባቸውን ወረዳዎች በመለየት በስድስት ዋና ዋና ተግባራት በመከወን ለማሳካት እቅድ ተይዛል፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃ 118 ወረዳዎች በዕቅዱ ውስጥ ተካተዋል፡፡ በእነዚህ ወረዳዎች ውስጥ የሚኖሩ ከ15 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ በእቅዱ መስረት በእነዚህ ወረዳዎች ላይ ለመተግበር ከታቀዱ ዋና ዋና ስራዎች መካከል፡ የበሽታ ቅኝትና አሳሳ ማጠናከር፡ የኣመራር ተሳትፎ ና የተቀናጀ አሰራር ማሻሻል፤ መከላከያ የኮሌራ ክትባት መስጠት፤የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ፡ የአካባቢ ና የግል ንጽህና አጠባበቅን በማሻሻል፡ ወረርሽኙ በሚከሰት ግዜ አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እና የማህበረሰብ ተሳትፎን በማሻሻል በሽታውን ከነዚህ ተጋላጭ ወረዳዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ታቅዳል፡፡
ባለፉት 3 ኣመታት የኮሌራ ወረርሽኝ ምላሽ የሚሆን ከ 10 ሚሊዮን ዶዝ በላይ ክትባት ለ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች ተደራሽ ተደርጎል፡፡
በእነዚህ ተጋላጭ ወረዳዎች የምትኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ወረርሽኞችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ተሳታፊ እንድትሆኑና የመፀዳጃ ቤት በመስራት እና በአግባቡ በመጠቀም፣ የመመገቢያ፣ የመጠጫ እና የውሃ ማስቀመጫ እቃዎችን በንጹህ ውሃ በማጠብ እና ከድኖ በማስቀመጥ ከዝንቦችና ከበካይ ነገሮች በመጠበቅ፣ ለማንኛውም አገልግሎት የሚውልን ከጉድጓድ፣ ከምንጭ፣ ከወንዝ እና ከመሳሰሉት የተቀዳ ውሃን በማከም ወይም በማፍላት በመጠቀም፣ ምግብ ከማዘጋጀት፣ ከማቅረብ፣ ከመመገብ በፊት፣ ከመፀዳጃ ቤት መልስ እና ሕፃናትን ካፀዳዱ በኋላ እጅን በመታጠብ፣ ምግብን በሚገባ አብስሎ በመመገብ፣ ከድኖ እና በንጹህ ቦታ በማስቀመጥ ከዝንቦችና ከሌሎች ነፍሳት ንክኪ በመጠበቅ ራሱንና ቤተሰቡን ከኮሌራ በሽታዎች በመከላከል የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ና የኮሌራን ማፍፊ እቅድ እንድናሳካ ጥሪ አቀርባለሁ፡፡
ኮሌራን እንግታ ! End Cholera!
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር
ታህሳስ 17 /2015 ዓ.ም