የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሲዳማ ክልል ተጀመረ
August 14, 2023
በዘመቻው ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይ እንደተገለፀው በወረዳው 81 ሰዎች በበሽታው ተጠቅተው የነበረ ሲሆን ሁሉም በወረዳው በተቋቋሙት ሶስት የኮሌራ ህክምና ማእከሎች ህክምና አግኝተው በአሁኑ ወቅት በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም በወረዳው ባለፉት 16 ቀናት በሽታው ሪፖርት አልተደረገም።
በዚህ ዙር እነደሀገር ክትባቱ ከአንድ አመት እድሜ በላይ ለሆኑ 2.3 ሚሊዮን ዜጎች የሚሰጥ ሲሆን በወረዳው የሚሰጠው 90 ሺህ ዶዝ መሆኑ ተገልጿል።
በስነ ስርአቱ መጨረሻም የወረዳው ጤና ጣቢያ ተጎብኝቷል።